
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 21/2017(ኢዜአ)፦በማዕድን ዘርፍ ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ እያስገኙ መሆናቸውን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኘ ገለጹ።
የማዕድን ሚኒስቴር ለማዕድን ዘርፍ የሚውሉ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 29 ተሽከርካሪዎችን እና 81 ላፕቶፖችን ለክልሎች ድጋፍ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ድጋፍ ያደረገው ለክልሎች፣ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ለኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት እና ለማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ነው፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ ንብረቶቹን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ ድጋፉ የተደረገው በበጀት ዓመቱ ከማዕድን ዘርፍ የተገኘውን ስኬት መሰረት በማድረግ ውጤቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ነው።
ለክልሎች የተደረገው ድጋፍ የማዕድን ዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተዋል።
ሚኒስቴሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተለያዩ ማዕድናትን ለውጭ ገበያ በመላክ አበረታች ለውጥ ማስመዝገቡን ገልጸዋል ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ሞርካ በበኩላቸው፤ የተደረገው ድጋፍ ከዚህ በፊት ያጋጥማቸው የነበረውን የተሸከርካሪ ችግር በማቃለል ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ነው የገለጹት።
የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን ሃለፊ የጽህፈት ቤት ሃላፊ ታደሰ ተሾመ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ የማዕድን ልማት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅና ድጋፍ የሚፈልግ ነው።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026