አምቦ፤ ሐምሌ 18/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮ ኮደርስ ዲጂታል ስልጠና በፊት ያለንን የቴክኖሎጂ እውቀት እና ክህሎት ለማዳበር ረድቶናል ሲሉ በምዕራብ ሸዋ ዞን ሰልጣኝ መንግስት ሰራተኞች ገለፁ።
የኢትዮ ኮደርስ ዲጂታል ስልጠና የተከታተሉና ኢዜአ ያነጋገራቸው የመንግስት ሰራተኞች እንዳሉት ስልጠናው ዘመናዊ የዲጂታል መሣሪያዎችን በተግባር ለማዋል በማስቻሉ ክህሎታቸውን በማሳደግ ውጤታማ የሚያደርግ ነው።
ከሰልጣኖች መካከል አቶ ደረጀ ፍቃዱ ፤ ስልጠናውን በመውሰዳቸው በጣም መደሰታቸውን ተናግረው፣ ሰራተኞችና ወጣቶች ችሎታቸውን ለማሳደግና አዳዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ስልጠናውን መከታተል እንደሚገባ አንስተዋል።
ሌላው ሰልጣኝ አቶ ራፌራ ደበሳ በበኩላቸው፤ በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን ስልጠናውን መውሰዳቸው እንዳስደሰታቸው ጠቅሰው በዚህም የነበራቸውን ክህሎትና ዕውቀት እንዳዳበረላቸው ተናግረዋል።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወሰደችው ወጣት ገላኔ መልካ በበኩሏ፤ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ዘመኑ ራሷን ብቁ በማድረግ ተወዳዳሪ ለመሆንና የቴክኖሎጂ ክህሎቷን ለማዳበር እንዳስቻላት ተናግራለች።
የምዕራብ ሸዋ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ አዲሷ ሻንቆ፤ በዞኑ በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ለመንግስት ሰራተኞችና ወጣቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን ለማዳበር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
ስልጠናው የቴክኖሎጂ ትስስር በመፍጠርና የወጣቶችን አቅም በማሳደግ እንዲሁም አዳዲስ ስራ ለመፍጠር አይነተኛ ሚና ያለው መሆኑን ጠቅሰው በዞኑ ፍላጎት ያላቸውን የህብረተሰብ አካላት ለማሰልጠን ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
ስልጠናው በቴክኖሎጂ የበቃ ዜጋን ለመፍጠር አጋዥ በመሆኑ በተለይም ወጣቶች መንግስት ያመቻቸውን እድል በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
በምዕራብ ሸዋ ዞን በ2017 በጀት ዓመት 29 ሺህ የመንግስት ሰራተኞችና ወጣቶች ስልጠናውን በበየነመረብ በመሰልጠን የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025