አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2017(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዳስትሪ ፓርኮች 16 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው ተኪ ምርት ማምረት መቻሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 65 በመቶ ማሳደግ ችሏል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ ዘመን ጁነዲ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሀገሪቱ ያሉት ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች 16 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው ተኪ ምርት ማምረት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊትና የሌሎች የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብሶች ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉን ጠቁመው፤ ይህም ኢንዱስትሪዎቹ በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ዕድል እንዲያገኙ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ45ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
በልዩ የኢንዱስትሪ ዞኖቹ በፋርማሲቲካል፣ በኮንስትራክሽን እና የኬሚካል ኢንዱስትሪ ዘርፎችን ተኪ ምርቶችን በስፋት ለማምረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ጨርቃጨርቅን ጨምሮ፣ የግብርና ምርት ማቀነባበር፣ የፋርማሲቲካል፣ የኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎችም እየተስፋፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው፤ አሁን ላይ ከ50 በመቶ በላይ መድረሱንም ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ የዓለም ሀገራት ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን በተመለከተ የግንዛቤ ስራዎች በመሰራታቸው ተጨባጭ ለውጦች ማምጣት መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በመላው ኢትዮጵያ ከሚያስተዳድራቸው 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል 11 የሚሆኑት ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን መሸጋገራቸው ይታወቃል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025