ደብረ ብርሃን፤ ሐምሌ 14/2017(ኢዜአ)፦ በደብረ ብርሃን ከተማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 25 ኢንዱስትሪዎች ወደማምረት መሸጋገራቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው የ2017 ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸምን የሚገመግምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ላይ ያተኮረ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።
የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርሃን ገብረህይወት እንደገለጹት በከተማው የሚከናወኑ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ሥራዎች ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ሚና አላቸው።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዘርፉን ለማጠናከር በተደረገ ጥረት በከተማው 25 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 232 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመው፣ ባለሀብቶቹ ወደሥራ ሲገቡ ከ21 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራሉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን መሰረት በማድረግ በተካሄደ ጥረትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከውጭ የሚገባን ተኪ ምርትና ለወጭ ንግድ የሚሆኑ ምርቶችን በማምረት ለገበያ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከልም አቶ አየለ ደስታ እንደገለጹት በአካባቢው በኢንዱስትሪና በኢንቨስትመንት ዘርፍ የታየው መነቃቃት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ነው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ ጽጌ ዋሪ በበኩላቸው በአካባቢው ያለውን ጸጋ ለማስተዋወቅ የተሰራው ሥራ የባለሀብቶች ፍሰት እንዲጨምር ማስቻሉን ተናግረዋል።
በደብረ ብርሃን ከተማ በበጀት ዓመቱ በኢንቨስትመንት ዘርፍ በአጠቃላይ ለ5 ሺህ 113 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ከመምሪያው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025