አዲስ አበባ፤ሐምሌ14/2017(ኢዜአ)፡-የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የእንሰት ልማት ፍላግሺፕ ፕሮግራም በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ለኢኮኖሚ እድገትና ለምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትና ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።
ብሔራዊ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የእንሰት ፍላግሺፕ ፕሮግራም ማብሰሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ግብርናው ለጠቅላላ ዓመታዊ ምርት፣ለአግሮ ኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት እና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ካለው ከፍተኛ አስተዋፅኦ በተጨማሪ በርካታ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አስችሏል፡፡
በመሆኑም የግብርና ልማቱን በተሻሻለ ቴክኖሎጂ እና ዕውቀት መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ የሪፎርም ስራዎችን በማከናወንና የዘርፉን ፀጋዎች በመጠቀም በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል።
በዚህም የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል ሀገራዊ አጀንዳዎችን ለማሳካት ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የሆርቲካልቸር ንኡስ ዘርፍ ካለው ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አኳያ ቀጣይ የትኩረት ማዕከል መሆኑን አመላክተዋል።
የሆርቲካልቸር ንዑስ ዘርፍ የምግብና የሥርዓት-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ለአብነት በ2016/17 ዓ.ም ወደ ውጭ ከተላከ 286 ሺህ ቶን የሆርቲካልቸር ምርት 565 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን አስታውቀዋል።
በመሆኑም የሆርቲካልቸር ንኡስ ዘርፍ የምርምርና ኤክስቴንሽን ስራን በማጠናከር እና የድህረምርት አያያዝና የገበያ መሰረተ ልማቶችን በማሻሻል ለሀገራዊ ኢኮኖሚያለውን አስተዋፅኦ ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ለዚህ የሚረዳ ሀገራዊ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የእንሰት ልማት ፍላግሺፕ ፕሮግራም ሰነድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ስትራቴጂው በሆርቲካልቸር ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም በሚፈለገው ደረጃ በመጠቀም ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ለምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትና መረጋገጥ የጎላ ሚና እንደሚያበረክትም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025