አሶሳ፤ ሐምሌ 13/2017(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተያዘው የመኸር ወቅት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
በክልሉ በመኸር እርሻ ከሚለማው መሬት ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱም ተመላክቷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ አቡራሞ ወረዳ አንጉላሎ ቀበሌ ከ3 ሺህ 200 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ በኩታ-ገጠም እየለማ ያለ የበቆሎ ማሳን ዛሬ ተመልክተዋል።
አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንደገለጹት አርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ የግብርና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
የአርሶ አደሩ በኩታ ገጠም የማልማት ልምዱ እያደገ መሆኑን ጠቁመው፣ በተያዘው የመኸር ወቅት ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
እስካሁንም ከ1 ሚሊዮን 500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን አቶ አሻድሊ ጠቁመው፣ ከመኸር እርሻ ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል።
የዘንድሮው የመኸር እርሻ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልጸው፣ በክልሉ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በርብርብ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወረዳው የመኸር እርሻ እንቅስቃሴን ከመመልከት ጎን ለጎን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025