ገንዳ ውሃ ፤ሃምሌ 3/2017 (ኢዜአ) ፡-በምዕራብ ጎንደር ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከእጣንና ሙጫ ሽያጭ ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የምዕራብ ጎንደር ዞን የአካባቢና ደን ጥበቃ ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የአካባቢ የህግ ተከባሪነትና የማህበረሰብ ተፅዕኖ ግምገማ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ አድጎ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ ከፍተኛ የሆነ የእጣንና የሙጫ ደን ሀብት አለ።
በዞኑ ከሚገኘው 760 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ በደን የተሸፈነ መሬት ከ234 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው በእጣንና ሙጫ ዛፍ የተሸፈነ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ17 ማህበራትና ባለሃብቶች 5 ሺህ 80 ኩንታል ምርት በመሰብሰብና ለገበያ በማቅረብ ከ108 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
አምራቾች ካገኙት ገቢ በተጨማሪ በሮያሊቲ ታክስ ክፍያ ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገኘታቸውን አስረድተዋል።
በዘርፉ ለ722 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸው መሆኑን ጠቁመው ይህም ዘርፉ ከገቢ ባሻገር ዋና የስራ እድል መፍጠሪያ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን ገልፀዋል።
በዞኑ በመተማ፣ በቋራና በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች የተመረተው የእጣንና ሙጫ ምርት በላኪዎች በኩል ወደ ውጭ ተልኮ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመተማ ወረዳ ሌንጫ ቀበሌ አዲስ ህይወት የህብረት ስራ ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በየነ ውቤ እንዳሉት ማህበሩ 60 አባላቱን በማሳተፍ በበጀት ዓመቱ 229 ኩንታል እጣንና ሙጫ ማምረት ችሏል።
ያመረቱትን እጣንና ሙጫ አንዱን ኩንታል በ53 ሺህ ብር በጨረታ በመሸጥ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የእጣን ዛፉ ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጥም ባገኙት ስልጠናና ግንዛቤ ፈጠራ በመመስረት በማምረት ሂደትና ከምርት በኋላ ተገቢውን እንክብካቤ እያደረጉ መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚሁ ወረዳ የላይኛው ለምለም ተራራ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ማህበር አባል አቶ ሙሀመድ አደም በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ 109 ኩንታል ምርት በመሰብሰብ ለገበያ አቅርበው በመሸጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ማህበራቸው 190 አባላት ያለው ሲሆን በቀጣይ የተሻለ ምርት ለማምረት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የእጣንና ሙጫ ደንን ለማስፋፋት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025