ሰመራ ፤ሐምሌ 3/2017 (ኢዜአ)፡- በአፋር ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አወል አብዱ የበጀት ዓመቱን የገቢ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸው፤ በዚህም ከዕቅድ በላይ 6 ቢሊዮን 40 ሚሊዮን 398 ሺህ 943 ብር መሠብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 46 በመቶ ልዩነት ያለውና 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
ገቢው የተሰበሰበው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክሰና ታክሰ ካልሆኑ የገቢ አርዕሰት መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።
ለበጀት ዓመቱ ከዕቅድ በላይ ክንውን ተከታታይነት ያለውና በየደረጃው ያሉ የአመራርና የዘርፉ ባለሙያዎች ቁርጠኝነት የታከለበት ስራ በመከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ ደረሰኝ ካለመቁረጥ ጀምሮ በህገ ወጥነት የተሳተፉ ከ1 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም አቶ አወል አስታውቀዋል።
አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የስነ-ምግባር ጥሰቶችን በማረም ህገ ወጥነትን ወደ ህግ የመመለስ ስራዎች መከናወኑንም አክለዋል።
ክልሉ ካለው እምቅ አቅም ጋር የተመጣጠነ ገቢ ለመሰብሰብ በቀጣዩ ዓመት ትኩረት የተሰጠ መሆኑንም አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025