ጎንደር፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፡- በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ወደ ብልፅግና ለሚደረገው ፈጣን የእድገት ጉዞ ምቹ መደላድል መፍጠራቸው ተገለጸ።
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የተውጣጡ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በጎንደር ከተማ ተገኝተው በፌደራልና በክልሉ መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት፣ የኮሪደር ልማት፣ የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና የጥገና ስራ እንዲሁም የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ከጎብኚዎቹ መካከል በብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ኝጉዋ ጋለ (ዶ/ር) በሰጡት አስተያየት፤ በፓርቲው የሚመራው መንግስት የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች በተግባር ምላሽ በመስጠት በኩል በጎንደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች አንዱ ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡
በተለይ ላለፉት 16 ዓመታት ሲጓተት ቆይቶ ኋላ ላይ ግንባታው ቆሞ የነበረውን የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት በለውጡ መንግስት ዳግም በማስጀመር በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተደረገ የሚገኘው ርብርብ ለሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ አበረታች ተግባራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት ሞዴልና ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው ያሉት በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ ናቸው፡፡
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የፓርቲው ራዕይና እሳቤ መገለጫ ከመሆናቸውም በላይ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥኑ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በፓርቲው የድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደረጀ ጸጋዬ በበኩላቸው፤ በጎንደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት የከተማውን ቱሪዝምና ኢንቨስትመንት የሚያነቃቁ እንደሆኑ መገንዘብ ችያለሁ ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ የከተሞች ታሪክ ጎንደር ገናና ስም ያላት የስልጣኔ በር ከፋች ከተማ ናት ያሉት አቶ ደረጀ፤ ዛሬም ያገኘቸው የልማት እድሎች ታሪኳን የሚያድስና ወደ ዘመናዊ ከተማነት የሚያሸጋግራት መሆኑዋን አረጋግጫለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሕዝቡ የእንግዳ ተቀባይነትና አክባሪነት ባህላዊ እሴት የአብሮነትና የአንድነት መገለጫ ሆኖ መቀጠሉን በጎንደር መመልከታቸውን አስረድተዋል።
እንደ ጎንደር ሁሉ በሌሎች የሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለሚደረገው ፈጣን የእድገት ጉዞ መደላድል የሚፈጥሩ መሆናቸውን አመራሮቹ ገልጸዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው፤ ከተማዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኘቻቸው የልማት እድሎች ከ15ሺ ህ በላይ ለሚሆኑ ሥራ አጥ ወገኖች የስራ እድል መፍጠር ያስቻሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሕዝቡ ለሰላም መከበርና ለልማቱ መጠናከር ግንባር ቀደም ባለቤት በመሆን ያደረጋቸው ተሳትፎዎች በፌደራልና በክልሉ መንግስት ድጋፍ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ስኬታማ እንዲሆን አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡
ከተለያዩ ክልሎች ተውጣጥተው ወደ ከተማዋ የመጡ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በመንግስትና በሕዝቡ ቅንጅት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን ለመመልከት እድል የፈጠረና ለወደፊት ሥራ በቂ ግብአት መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
በልማት ፕሮጀክቶቹ ጉብኝት ላይ የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማን ጨምሮ ከሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025