አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ366 ሺህ ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት ለዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ሲሰራ ቆይቷል።
በ2017 በጀት ዓመት መጀመሪያ በአዲስ አበባ ለ300ሺህ ስራ ፈላጊዎች በፍትሃዊነት የስራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰዋል፡፡
በዚህም ቢሮው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ አንድ ሚሊየን በላይ ከሆኑ ስራ ፈላጊ ወጣቶችና ወላጆች ጋር ውይይት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።
ስራ ፈላጊዎችን በፍትሃዊነት ለመቀበል በተሰራው ስራ 403ሺህ ዜጎችን በኦን ላይን በመመዝገብ በበጀት ዓመቱ ለ366ሺህ 44 ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል በመፍጠር አፈጻጸሙን ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
የስራ "ድል ከተፈጠረላቸው መካከል 55 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውም ጨምረው ተናግረዋል።
ለወጣቶቹ በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በንግድና ሌሎች ዘርፎች የስራ ዕድል በመፍጠር በቅጥርና በማደራጀት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር እንደመሆኗ ይህንኑ ኃይል ወደ አምራችና አልሚነት መቀየር ተገቢ መሆኑን ነው የተናገሩት።
አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከማድረግ ባሻገር ለስራ ፈላጊ ወጣቶች በርካታ የስራ ዕድሎች መፈጠራቸውን ጠቅሰው፤ ወጣቶች ዕድሉን በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውንና ሀገራቸውን በኢኮኖሚ ማበልጸግ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በበኩላቸው፤ የተፈጠረላቸው የስራ ዕድል ራሳቸውን ለመለወጥ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራው የባህሩና ጓደኛሞቹ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ወጣት ባህሩ ፈየራ እድሉን ከማግኘቱ በፊት በተመረቀበት ሙያ ስራ ማግኘት ባለመቻሉ የቤተሰብ ጥገኛ እንደነበር አስታውሷል።
መንግስት ባመቻቸው ዕድል በመጠቀም የመስሪያ ሼድ እና የገንዘብ ብድር በማግኘቱ ቋሚ የስራ ዕድል ተፈጥሮለት ስራ በመጀመሩ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።
ወጣት ሆኖ የሰራ ቅጥር ከመጠበቅ አማራጭ የስራ ዕድሎችን በአግባቡ በመጠቀም የተሻለ ገቢ ማግኘት ይቻላል ያለችው ደግም በከብት ማድለብ ስራ ላይ የተሰማራችው ወይዘሮ ስለእናት ታፈሰ ናት።
ወጣቶች በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ በተፈጠረው የስራ ዕድል መጠቀም አለባቸው ያለን ደግሞ የስራ ዕድል የተፈጠረለት ወጣት ዮናስ ደምሴ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025