
ወላይታ ሶዶ ፤ሰኔ 30/2017 (ኢዜአ)፡-የህዝብን ሁለንተናዊ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የገቢ አቅምን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አመለከተ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስትቲዩት ከባለድርሻ አካላት ቢሮዎች ጋር በመተባበር በክልሉ 11 ከተሞች ላይ የገቢ አቅምን በተመለከተ ባካሄደው ጥናት ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ከተማ ውይይት ተካሄዷል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ እና የአማካሪዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ቦሻ ቦምቤ (ዶ/ር)፤ በክልሉ ያለውን የገቢ አቅም ለመለየት የሚያስችል ጥናት መካሄዱን ተናግረዋል።
በጥናቱ መሰረትም የክልሉን 75 በመቶ ወጪ በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል አቅም መኖሩን መለየት መቻሉን ጠቅሰው ጥናቱ የገቢ አማራጮችንና የማደግ ተስፋን፣ ማነቆዎችንና መፍትሄዎችን ያመላከተ መሆኑንም ተናግረዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት የገቢ አቅም መጨመሩ የተመላከተ ቢሆንም በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ያህል ገቢ እየተሰበሰበ አለመሆኑም ታይቷል ነው ያሉት።
በመሆኑም በጥናቱ የተገኘውን የመፍትሄ ሃሳብና ምልከታዎች ተግባራዊ በማድረግ የገቢ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም ክልሉ በራሱ ገቢ ወጪውን የሚሸፍንበትን እድል መፍጠር ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ በየነ፤ የክልሉን ህዝብ ሁለንተናዊ የልማት ጥያቄ ለመመለስ ይቻል ዘንድ የገቢን አቅም ማሳደግ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።
በዘርፉ የተለያዩ ማነቆዎች ቢኖሩም የገቢ መጠን እያደገ መምጣቱን ጠቁመው የመደበኛ እና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎችን ይበልጥ ለማሳደግ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በጥናቱ ያልታዩ የገቢ ምንጮችንም ጭምር በመቃኘት ገቢ የመሰብሰብ አቅምን በማሳደግ ልማትን ማስቀጠልና የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት፣ የገቢዎች ቢሮ፣ የፋይናንስ ቢሮ፣ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ እና የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026