የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የተገነባልን የመስኖ መሰረተ ልማት ልማቱን በስፋት ለማከናወን ያግዘናል - አርሶ አደሮች

Jul 8, 2025

IDOPRESS

አሶሳ፤ ሰኔ 30/2017(ኢዜአ)፦ የተገነባልን የመስኖ መሰረተ ልማት ልማቱን በስፋት ለማከናወን ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኡራ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ በ74 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የፀንፀሀሎ የመስኖ መሠረተ ልማት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን በተገኙበት ተመርቋል።

የመስኖ ፕሮጀክቱ 200 ሄክታር ማሳ ማልማት የሚችልና ከ800 በላይ የሚሆኑ የሶስት ቀበሌ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች የመስኖ መሠረተ ልማቱ ከዚህ በፊት የሚያከናውኑትን የመስኖ ልማት ለማስፋፋት እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል።

አርሶ አደር ሙሀመድ ሙዘሚል እና ዳውድ አጣሂር ከዚህ በፊት በአነስተኛ የመስኖ ስራ ሲጠቀሙ ቢቆዩም ብዙም ውጤታማ እንዳልነበሩ ገልፀዋል።

አሁን ላይ የተጠናቀቀው የመስኖ መሰረተ ልማት ከፍተኛ ርዝመት ያለው የውሀ መውረጃ ቦይ ያለውና ውሀን በሁሉም አቅጣጫ ተደራሽ ማድረግ የሚችል በመሆኑ የመስኖ ልማቱን በስፋት ማከናወን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላው ወጣት አርሶ አደር አብዱ አልቃዲ በበኩሉ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታው ከመደበኛ የግብርና ስራችን በተጨማሪ በመስኖ ልማት እንድንሳተፍ እና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ነው ብሏል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ባበክር ሀሊፋ በበኩላቸው በክልሉ በዘንድሮው በጀት ዓመት የ11 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

አርሶ አደሩ በመስኖ ልማት ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸው የመስኖ መሰረተ ልማቱን በመጠቀም የበለጠ ምርታማ መሆን እንደሚቻል ተናግረዋል።

የፀንፀሀሎ መስኖ መሰረተ ልማት ሰፊ የማልማት አቅም ያለው በመሆኑ አርሶ አደሩ በኩታ ገጠም የተለያዩ የሰብል አይነቶችን በማምረት ተጠቃሚ እንደሚሆን አስታውቀዋል።

የመስኖ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ የላቀ እንደነበር የገለጹት ደግሞ ግንባታውን ያከናወነው ወርቅነህ ግዛው የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ስራ አስኪያጅ ወርቅነህ ግዛው ናቸው።

የመስኖ ፕሮጀክቱ ለአሳ እርባታና ለሌሎች የግብርና ስራዎች ምቹ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025