ባህርዳር፤ ሰኔ 30/2017 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረትን ለማቃለል ከ15 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ምርጥ የሰብል ዘር ለማባዛት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
ቀደም ሲል የተባዘው ምርጥ የሰብል ለ2017/2018 የምርት ዘመን ልማት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ ተመልክቷል።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የዘር ብዜት ባለሙያ አቶ ጥላዬ ሞገሴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የዘር አቅርቦት እጥረት ለማቃለል በምርት ዘመኑ በሁለት የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ በ10 ዩኒየኖችና በ34 የግል ዘር አብዥዎች እየተከናወነ ይገኛል።
እስካሁን በተደረገው የዘር ብዜት እንቅስቃሴም በዕቅድ ከተያዘው መሬት 2 ሺህ 595 ሄክታሩ በበቆሎና ስንዴ ዘር ብዜት መሸፈኑን ተናግረዋል።
ቀሪው መሬት በቀጣይ እንደየዘር ወቅቱ የማባዛት ስራውን በማጠናከር የክልሉን የዘር አቅርቦት እጥረት ለማቃለል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ተግባር ላይ እንደሚውል አስረድተዋል ።
ከዚህም ከ400 ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላ፣ጤፍ፣ ሰሊጥና አኩሪ አተር ምርጥ የሰብል ዘር እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
በኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአየሁ እርሻ ልማት ስራ እስኪያጅ አቶ ማስረሻ እንግዳ እንዳሉት፤ ድርጅቱ በ1 ሺህ 75 ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ ማከናወን ጀምሯል።
በዚህም "ዜድ ኤስ ኤም 721" የተሰኘ የተሻለ አዲስ የበቆሎ ዝርያ በማመቻቸት በ350 ሄክታር መሬት ላይ ዘር እያባዙ መሆኑን አመልክተዋል።
እንዲሁም ድርጅቱ ከአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝና ከኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር ውል በመውሰድ ''ቀቀባ፣ ዳንፌና ኦጎልቾ'' የተሰኙ የስንዴ ዝርያዎችን በ725 ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ለማከናወን የእርሻ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በምርት ዘመኑ በ50 ሄክታር መሬት ላይ "ቢኤች 661" የተሰኘ የበቆሎ ዘር ብዜት እያከናወኑ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በምዕራብ ጎጃም ዞን በግል ዘር በማባዛት የተሰማሩት አቶ ቢኒያም ሙላት ናቸው።
ባለፈው ዓመት በዘር ከተባዛው መሬት ከ281 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ የሰብል ዘር ተሰብስቦ ለ2017/2018 የምርት ዘመን ልማት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝም የግብርና ቢሮው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025