የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በደቡብ ወሎ ዞን ከሰብል ልማት በተጓዳኝ በፍራፍሬ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል

Jul 8, 2025

IDOPRESS

ደሴ ፤ ሰኔ 30 /2017 (ኢዜአ)፦ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተሰማሩበት የፍራፍሬ ልማት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን የደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።

በዞኑ ቃሉ ወረዳ የቀበሌ 06 ነዋሪ አርሶ አደር አብዱ ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ከሰብል ልማት ሥራቸው በተጨማሪ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ እየሆኑ መጥተዋል።

መንግስት ለአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የሰጠው ትኩረት በየዓመቱ የቆላ ፍራፍሬ ችግኝ በስፋት ለመትከል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸው፣ ከፍራፍሬ ምርታቸውም ሽያጭ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

በእርሻ ማሳቸው ዙሪያ ካለሙት የማንጎ፣ ፓፓያና ሌሎች ፍራፍሬዎች ምርት ሽያጭ በዘንድሮ ዓመት ብቻ ከ200 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።


የፍራፍሬ ልማት ሥራቸውን ለማሳደግም በተያዘው የክረምት ወራት ተጨማሪ የፍራፍሬ ችግኝ በመትከል የተሻለ ገቢ ለማግኘት ጠንክረው እንደሚሰሩ ነው የገለጹት።

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የቀበሌ 07 ነዋሪ አርሶ አደር ኢብራሂም አደም በበኩላቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸውን የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል ገቢያቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በሩብ ሄክታር መሬታቸው ላይ ማንጎ፣ ሙዝ፣ ብርቱካንና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞችን መትከላቸውን አስታውሰው፣ ለችግኞቹ ተገቢ እንክብካቤ በማድረግ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዘንድሮ ከፍራፍሬ ምርት ሽያጭ ከ160 ሺህ ብር በላይ ገቢ አግኝቺያለሁ ያሉት አርሶ አደሩ፣ በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ነጋዴዎች ማሳቸው ድረስ መጥተው ምርታቸውን መግዛታቸው ድካማቸውን መቀነሱን ተናግረዋል።

ተጠቃሚነታቸውን ዘላቂ ለማድረግ በዘንድሮው ክረምትም ከ300 በላይ የቆላ ፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።


በደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውሃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ አሳልፍ አህመድ በበኩላቸው፣ አርሶ አደሩ ከሰብል ልማት በተጓዳኝ እያከናወነ ባለው የፍራፍሬ ልማት ተጠቃሚ እየሆነ ነው ብለዋል።

የቆላና የደጋ ፍራፍሬ ችግኝ በመትከል የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ተጨማሪ ሃብት በመፍጠር ለኢኮኖሚ እድገት አሻራቸውን እያሳረፉ መሆኑንም አስረድተዋል።


በዞኑ ከ7 ሺህ 200 ሄክታር በላይ መሬት በፍራፍሬ መልማቱን ጠቁመው፣ በአማካይ ከአንድ ሄክታር መሬት ከ110 ኩንታል በላይ ምርት እየተገኘ መሆኑን አቶ አሳልፍ ጠቁመዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለፍራፍሬ ልማት በተሰጠው ትኩረትና በተደረገ ድጋፍ በሄክታር ከ40 ኩንታል በላይ ምርት ጭማሬ ለማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።


ለአርሶ አደሮች በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ምርታቸውን ከአካባቢው ባለፈ ለአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጭምር በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

እንደ ቡድን መሪው ገለጻ በዘንድሮ ክረምትም በ2 ሺህ 800 ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርም በዞኑ በአጠቃላይ ከ29 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025