አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የ2018 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት አጽድቋል።
ምክር ቤቱ 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
በስብሰባው ላይ የምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ የ2018 ዓ.ም የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት የውሳኔ ሀሳብ እና ሪፖርት አቅርበዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳቡን በመመርመር የ2018 የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀትን አፅድቋል።
በሪፖርቱ ላይ የቀጣይ በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊዮን ብር መሆኑ ተመላክቷል።
ከ2018 ረቂቅ በጀት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 415 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ወጪ፣ 315 ቢሊዮን ብር ለክልል መንግስታት ድጋፍ እንዲሁም 14 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ድጋፍ የሚውል ነው።
ከረቂቅ በጀቱ 1 ትሪሊዮን ብር ወይም 73 በመቶውን ከታክስ ገቢ 236 ቢሊዮን ብር ከልማት አጋሮች ቀሪውን ደግሞ ከፕሮጀክቶች ድጋፍና ልዩ ልዩ ገቢዎች ለማግኘት ታቅዷል።
በረቂቅ በጀቱ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት አንፃር ያልተጣራ የበጀት ጉድለት 2 ነጥብ 2 በመቶ እንዲሁም የተጣራ የበጀት ጉድለት 1 በመቶ መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።
መንግስት የበጀት ጉድለቱን በቀጥታ ከብሔራዊ ባንክ ብድር በመውሰድ ሳይሆን በግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ እንደሚሸፍንም ተጠቁሟል።
የ2018 ረቂቅ በጀት የተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን እና የ10 ዓመቱን መሪ የልማት እቅድ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተዘጋጀ እንደሆነም በሪፖርቱ ላይ ቀርቧል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025