የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

265 ሺህ ገደማ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Jul 4, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፦በአሁኑ ወቅት 265 ሺህ ገደማ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሔደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ መንግስት የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመፍታት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

የቤት ችግር ከፍተኛ ሥራ የሚፈልግ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ በመንግስት፣ በግል፣ በመንግስትና የግል ትብብር የመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታዎች እየተካሄዱ መሆኑን አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅትም 265 ሺህ ገደማ የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን ጠቁመው፤ መንግስት ከግል ባለሃብቱ ጋር በቅንጅት በመስራት የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት አንድ ሚሊዮን ያህል ቤቶች መገንባታቸውን አውስተው፤ የመኖሪያ ቤቱ ግንባታ ደረጃውን የጠበቀና ለኑሮ ምቹ የሆነ በማድረግ ረገድ ሰፊ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ከመኖሪያ ቤት ግንባታው ጎን ለጎንም ከ100 ሺህ ያላነሱ የመኖሪያ ቤቶች በክረምት በጎ ፈቃድ ጥገና የሚደረግላቸው መሆኑንም ነው ያነሱት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026