
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 21/2017(ኢዜአ)፦ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት ባለፉት ወራት 364ሺህ የንግድ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎትን በኦንላይን ማከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
70ሺህ አዳዲስ የንግድ ፈቃዶችን በኦንላይን መስጠቱን ቢሮው ገልጿል።
የንግድ ቢሮው ምክትል ኃላፊ ፍስሀ ጥበቡ ለኢዜአ እንዳሉት፥ በበጀት ዓመቱ ለንግዱ ማህበረሰብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የሚያሳልጡ ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል ብለዋል።
በወረዳና በክፍለ ከተማ በተበታተነ መልኩ የሚሰጠውን የንግድ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ማዕከል መስጠት የሚያስችል አደረጃጀት ለመፍጠር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት 411ሺህ የንግድ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ በአሥር ወራት ብቻ 364ሺህ የንግድ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በኦንላይን መከናወኑን ተናግረዋል።
ከ70ሺህ የማያንሱ አዳዲስ የንግድ ፈቃድ ምዝገባ አገልግሎት በኦንላይን መሰጠቱንም ነው ጨምረው የገለጹት።
ህገ-ወጥና ኢ-መደበኛ የንግድ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መልክ ለማስያዝ ስኬታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከሚወሰዱ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ባሻገር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ዘመናዊ የንግድ መስሪያ ቦታ በማዘጋጀት ወደ ህጋዊ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በኦንላይን ንግድ ፈቃድ ካደሱ ነጋዴዎች መካከል አቶ ፍስሃ ገብረመስቀል፥ ቀድም ሲል የነበረው የንግድ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት አሰጣጥ ምቹ እንዳልነበር በማስታወስ፥ አሁን ሁሉም ነገር ቀላል መሆኑን ተናግረዋል።
የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ንግድ ፈቃዳቸውን ማሳደስ በመቻላቸው ጊዜያቸውን ከመቆጠብ ባለፈ እንግልት እንዳስቀረላቸው ጠቅሰዋል።
አዲስ የንግድ ፈቃድ ማውጣትም ሆነ የእድሳት አገልግሎትን በዘመናዊ መንገድ መጀመሩ ጊዜውን የዋጀ እና ለህብረተሰቡም ፋይዳው የላቀ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ ይርዳው ምትኩ ናቸው።
ሌላኛዋ አስተያያት ሰጪ ወይዘሮ መቅድስ ታደሰ፤ ቀድም ሲል ንግድ ፈቃድ ለማደስ ረጅም ጊዜ ይወስድ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ በኦንላይን መደረጉ ተጠቃሚ አድርጎኛል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...
Apr 15, 2026
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026