የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ ሦስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት እያለማች ነው - ኢንስቲትዩቱ

Jun 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቆይታ ጊዜዋና በመረጃ መሰብሰብ የተሻለ አቅም ያላትን ሦስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት እያለማች መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ETRSS-01 እና ET-Smart-RSS የተሰኙ ሁለት የመሬት ምልከታ ሳተላይቶችን ከቻይና የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ሕዋ መላኳ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ETRSS-02 የሚል ስያሜ የተሰጣትን ሦስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት በቅርቡ እንደምታመጥቅ መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ ኢኒስቲትዩቱ የተለያዩ የሳተላይት መረጃዎችን በማደራጀትና በመተንተን ለሀገር ጥቅም እንዲውል እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት ሁለቱ ሳተላይቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ማሳካታቸውን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት።


ከሳተላይቶቹ የተገኙት መረጃዎች ለግብርና፣ ለቱሪዝም፣ ለመሬት አስተዳደር፣ ለተፈጥሮ ሀብት፣ ለአደጋ ስጋት ቅነሳ አና ለሌሎች ስራዎች በግብዓትነት መዋላቸውን አመልክተዋል።

ተቋማትም የወሰዷቸውን መረጃዎች ጥናትና ምርምርን ጨምሮ ለተለያዩ ስራዎቻቸው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

ሦስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ከ12 እስከ 18 ወራት ባለ ጊዜ ውስጥ ለማምጠቅ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

የሳተላይት ቁጥር መጨመር የመረጃ ግኝት እና ወቅታዊነቱም ጭምር እያደገ እንደሚሄድ አክለዋል።

በተለይም ሦስተኛዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ቀደም ሲል ከነበሩት የተሻለ አቅም ያላት፣ የቆይታ ጊዜዋም ከፍ ያለ እና የተሻለ መረጃ መስጠት የሚያስችል አቅም ያላት መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025