
ሀዋሳ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦በመንግስት ተቋማት የሚሰበሰቡ አስተዳደራዊ መረጃዎች ለስታስቲክስ ዓላማ መዋል እንዲችሉ በአግባቡ መመዝገብ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ከሲዳማ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ጋር በመተባባር በስታስቲክስ መረጃ አያያዝና አመራር ዙሪያ ለክልል ሴክተር አመራሮችና የመረጃ ባለሙያዎች በሃዋሳ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ጀሚላ መሃመድ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት፥ በመንግስት ተቋማት የሚሰበሰቡ አስተዳደራዊ መረጃዎች ለስታስቲክስ ዓላማ እንዲውሉ አድርጎ መመዝገብ ይገባል፡፡
አስተዳደራዊ መረጃዎች እንደሃገር ያለውን የስታስቲክስ መረጃ ክፍተት የሚሞሉ ቢሆንም በእስካሁኑ ሂደት በተገቢው ባለመደራጀታቸው በተፈለገው ልክ ለስታስቲክስ ዓላማ ያለመዋላቸውን አንስተዋል፡፡
በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍ በእቅድ ላይ የተመሰረተ ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የክልሎችን ስታስቲክሳዊ መረጃ አያያዝ የማሳደግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የመሬት ምዝገባ፣የግብርና ግብዓቶች ስርጭት፣የግብር፣ የገበያ ዋጋን ጨምሮ አስተዳደራዊና መሰረታዊ የስነ-ህዝብ መረጃዎችን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመሰብሰብ ወቅታዊ፣ትክክለኛና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን ማቅረብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አራርሶ ገረመው (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ቢሮው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና መልክዓ-ምድራዊ መረጃዎችን የመሰበሰብ፣ የማደራጀትና የመተንተን ኃላፊነቱን ለመወጣት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም የክልሉን የልማት እና እድገት ደረጃን የሚያሳዩ ጥናቶችን በማካሄድ ለፖሊሲ ግብዓት፣ ለእቅድ፣ ለጥናትና ምርምር የሚውሉ ወቅታዊ መረጃዎችን እያደራጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ የሚሰበሰቡ አስተዳደራዊ መረጃዎች ለስታስቲክስ ዓላማ እንዲውሉና ወቅታዊ፣ ትክክለኛና ተዓማኒ እንዲሆኑ የባለሙያውንና የአመራሩን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የሃዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አሰጋሽ አሰፋ፤ አገልግሎቱ ከሲዳማ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በመረጃ አያያዝና አመራር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከአራቱም ዞኖች ለተውጣጡ አመራሮችና የመረጃ ባለሙያዎች ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውም ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026