
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦ ባህርዳርን ወደ ምቹ የቱሪዝም፣ የአገልግሎትና የመኖሪያ ከተማነት ማሸጋገር የሚያስችሉ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሀርዳር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ባህርዳርን ወደ ምቹ ከተማነት ለማሸጋገር የሚረዱ የመንገድ ግንባታ፣ የኮሪደር ልማትና የተቋማት ዕድሳት ስራዎች በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውንም ገልጸዋል።

በከተማዋ የሚገኙ የአማራ ክልል መንግሥት ተቋማት ምቹ የሥራና የአገልግሎት ከባቢ በመፍጠር ላይ መሆናቸው የሚደነቅ ተግባር ነው ብለዋል።
ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለቱሪስቶች ተወዳጅና ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡

የተጀመሩ መልካም ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በተጨማሪም ፕሮጀክቶችን በጥራት ለማጠናቀቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
መንግስት የከተሞች ውበትና የተፈጥሮ ሀብቶች ተጠብቀው እንዲዘምኑና የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር ለሚከናወኑ ተግባራት ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026