
ጋምቤላ፤ግንቦት 27/2017 (ኢዜአ)፦የኮሪደር ልማቱን በማፋጠን ከተማዋን ለነዋሪዎቿና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገለጹ።
በከተማዋ በአራቱም አቅጣጫ የ14 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ ለማከናወን ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ሳይመን ሙን (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ከንቲባ ሳይመን ሙን (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የተጀመረውን የኮሪደርና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መሰረተ ልማት በማፋጠን ከተማዋን ለነዋሪዎቿና ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።
የጋምቤላ ከተማ ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረችና የንግድ ቀጠና የነበረች ታሪካዊ ከተማ ብትሆንም የእድሜዋን ያህል ያላደገችና የመንገድ መሰረተ ልማት ችግር ያለባት ከተማ መሆኗንም አስታውሰዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የከተሞች ልማት ስትራቴጂ ፖሊሲን ታሳቢ በማድረግ መንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮችን ለማሟላት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ የከተሞች የኮሪደር ልማትን በማጠናከር ከተማዋን ውብ፣ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በከተማዋ በመጀመሪያው ዙር በተለያዩ አቅጣጫዎች የ14 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ በአራት ምዕራፍ ተከፋፍሎ ለመገንባት ግብ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
በከተማው እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት የሥራ ዕድል ካገኙ ዜጎች መካከል ወጣት ሳዳም አብዱ በሰጠው አስተያየት፥ የኮሪደር ልማት ለከተማው እድገት ከሚኖረው ፋይዳ ባለፈ የሥራ እድል ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ተናግሯል።
ኮሪደር ልማት የአካባቢን ገጽታ ለመቀየርና ስራ አጥ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መርሃ ግብር መሆኑን የገለጸው ደግሞ ሌላው በከተማው ኮሪደር ልማት እየተሳተፈ ያለው ወጣት ኑርሴን አብዱልቃደር ነው።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026