የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትና በኮንስትራክሽን በርካታ የሥራ ዕድል እየፈጠረች ነው

May 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 19/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ የሥራ ዕድል እየፈጠረች መሆኗ የሚደነቅ ነው ሲሉ የዓለም ሥራ ድርጅት የሥራ፣ ልማትና ኢንቨስትመንት ክፍል ሃላፊ ሚቶ ትሱካሞቶ ገለጹ፡፡


ኢትዮጵያ 20ኛውን የዓለም ሥራ ድርጅት ቀጣናዊ ስብሰባ በብቃት በማስተናገድ በታዳሚዎች ዘንድ እውቅና ተችሯታል፡፡


በአዲስ አበባ የተገነቡ የአረንጓዴ ልማት፣የቱሪዝም ስፍራዎች፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት ኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ዘላቂ ልማት ትኩረት መስጠቷን አረጋግጠዋል፡፡


የዓለም ሥራ ድርጅት የሥራ፣ ልማትና ኢንቨስትመንት ክፍል ሃላፊ ሚቶ ትሱካሞቶ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ የሥራ እድል መፍጠሩን የሚደነቅ ነው፡፡


ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት ከስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ 17ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ስብሰባ ስታስተናግድ ነበር ያሉት ሃላፊዋ፤ አሁን አስደናቂ ለውጦችን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡


በአዲስ አበባ በርካታ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ገልጸው፤ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኢንቨስትመንትን በመሳብ ሰፊ የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ነው ብለዋል፡፡


የመሰረተ ልማት ዝርጋት ከፍተኛ የሆነ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም እንዳለው የገለጹት ሃላፊዋ፥ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከተሞችን የመገንባት ሂደት ላይ መሆኗን ተረድቻለሁ ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅት የሥራ ዕድል በሚፈጥሩ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ሀገራት የሚያደርገው ድጋፍ ተጠቃሚ እንደሆነች ገልጸዋል፡፡


የኮንስትራክሽን ሥራዎች የአካበባው ማህበረሰብ በባለቤትነት እንዲሳተፍበት የሚያደርግ መሆኑን በማንሳት፤ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ የተመለከትኩት ይሄን ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026