
ደብረ ማርቆስ፤ግንቦት 10/2017(ኢዜአ)፦አሲዳማ መሬትን በኖራ በማከም ለሰብል ልማት በማዋል የተሻለ ምርት እያገኙ መሆኑን በምስራቅ ጎጃም ዞን ኢዜአ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ገለጹ።
በዞኑ የ2017/18 የምርት ዘመን ከ248 ሄክታር በላይ መሬት በኖራ በማከም ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻከል ወረዳ አርሶ አደር በቃሉ ነጮ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በአሲድ የተጠቃ መሬታቸውን በማከም መዝራት ከጀመሩ ሶስት ዓመት ሆኗቸዋል።
በዚህም በሄክታር በፊት ያገኙት ከነበረው ከስድስት ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት ማግኘታቸውን ገልጸው፥ በዚህ ዓመት ይበልጥ ለማስፋት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሌላው በዞኑ የአነደድ ወረዳ አርሶ አደር አስማረ ምናሴ በበኩላቸው፥ ከአንድ ሄክታር በላይ የእርሻ ማሳቸው በአሲድ በመጠቃቱ የምርት መጠኑ ቀንሶ መቆየቱን አስታውሰው፥ አሁን ላይ በኖራ ታክሞ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል ብለዋል።
በዚህ ዓመት በግብርና በኩል የቀረበላቸውን ኖራ ከግማሽ ሄክታር በላይ የእርሻ ማሳቸው ላይ ቀድመው ከአፈሩ ጋር የማዋሃድ ስራ በመስራት ለዘር ማዘጋጀታቸውንም አስረድተዋል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ እንቢአለ አለኸኝ፤በ2017/18 የምርት ዘመን በዞኑ ከ248 ሄክታር በላይ አሲዳማ መሬት በኖራ በማከም ምርታማነቱን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህም ከ64 ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን ከ18 ሺህ 500 ኩንታል በላይ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።
በመጪው የመኸር ምርት ዘመን አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የግብርናውን ምርታማነት በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዞኑ 2017/18 የምርት ዘመን ከ25 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት ታቅዶ የእርሻና የዘር ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ ታውቋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026