
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በፎረሙ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና ሌሎች ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

የቢዝነስ ፎረሙ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በአጋር የልማት ድርጅቶች የተዘጋጀ ነው።
በተጨማሪም በፎረሙ የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ ኩባንያዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ አማካሪዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ታድመዋል።
ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ የቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ተቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከማድረግ ባለፈ ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት የመፍጠር አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
አዳዲስ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ማሳየት እና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማሳወቅ ከፎረሙ ዓላማዎች መካከል ይገኙበታል።
ዛሬና ነገ በሚካሄደው ፎረም በርካታ የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026