
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2017(ኢዜአ)፦በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች የአመራር ቁርጠኝነትና የመተባበር ውጤትን በተግባር ያሳዩ ናቸው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ።
አዲስ አበባ የዓለም የዲፕሎማሲ መዲና፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ እንቅስቃሴ ማዕከል መሆኗን ተከትሎ ከተማዋን የሚመጥን የልማት ስራ በሰፊው በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በከተማዋ እየተካሔደ ያለው የኮሪደር ልማት በአገር አቀፍ ደረጃ ጥሩ መነቃቃት የፈጠረ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ነው።

የኮሪደር ልማት ዜጎችን ወደ ዘመናዊ አኗኗር በማሸጋገር የከተሞች ተወዳዳሪነት እንዲጨምር ከማድረጉ ባሻገር እንደ አገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውም የጎላ ነው።
ኢዜአ በመዲናዋ በተለያዩ የኮሪደር ልማት ስፍራዎች አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች እንደገለጹት የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን አጎናጽፏታል።
በኮሪደር ልማት የተከናወኑ መሰረተ ልማቶች ሳቢና ምቹ ከመሆናቸው ባሻገር አማራጭ የመዝናኛ ስፍራዎችን መፍጠራቸውን ነው የተናገሩት።

የከተማዋን ውበት የሚጨምሩ የመንገድ መሰረተ ልማቶች፣ የመዝናኛ ሥፍራዎችና ማረፊያዎች መኖራቸው ከተማዋ እያደገችና ተወዳዳሪ እየሆነች መምጣቷን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።
ለ18 አመታት ኑሯቸውን በኖርዌይ ያደረጉት ወይዘሮ አምሳለ መላከብርሃን እንደገለጹት በአዲስ አበባ በየወቅቱ የሚታዩት አዳዲስ ልማቶች ግርምትን የሚፈጥሩ ናቸው።
በተለይም የኮሪደር ልማቱና የዚሁ አካል የሆኑ የልማት ስራዎች መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረትና ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ በመሆኑ በእጅጉ መደሰታቸውነ ገልጸው ስራው እንደ አገር የሚያኮራ ተግባር ነው ብለዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ኤልያስ ኦኩማ በበኩላቸው የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ዘመናዊነትን እያላበሳት መሆኑን መስክረዋል።
ለዜጎች ምቹ ስፍራንና ሁኔታን ለመፍጠር መንግስት ያሳየው ቁርጠኝነት በእጅጉ የሚደነቅና የሚያስመሰግን መሆኑንም ገልጸዋል።
በመሆኑም ጎብኚዎች አዲሲቷን ኢትዮጰያ መጥተው እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም የኮሪደር ልማቱ አማራጭ የመዝናኛ ስፍራዎችን የፈጠረ በመሆኑ ሰዎች የእረፍት ጊዜያቸውንና የተለያዩ ኹነቶቻቸውን በቀላሉ ለማሳለፍ ምቹ እድል እንደተፈጠረላቸው አክለዋል።

ወይዘሮ መዲና ዑመር የተባሉ አስተያየት ሰጪ እንደገለጹት የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር በዘለለ አዳዲስ የመዝናኛና የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች እንዲገነቡ እድል ፈጥሯል።
በሁሉም መስክ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ካላቸው ፋይዳ በዘለለ ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉና የበለጸገች አገር የማውረስ ተልእኮን የሚያሳኩ ናቸው ያሉት ደግሞ አቶ ስንታየሁ ደንድር ናቸው።

ቀደም ሲል ህጻናትን ለማጫወትና ለማዝናናት በቂ ስፍራዎች እንዳልነበሩ ጠቁመው የኮሪደር ልማቱ አካል የሆኑ የመዝናኛ ስፍራዎች በቀላል ዋጋና በቅርቡ መኖራቸው እንዳስደሰታቸው ጠቁመዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026