
አርባ ምንጭ፤ ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ከተሞች ልምዳቸውን በመለዋወጥ ለእድገታቸው የተሻለ ግብዓት እያገኙበት መሆኑን ገለጹ።
በኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ አዘጋጅነት የአራት ክልሎች ከተሞች ከንቲባዎች የተሳተፉበት ስልጠናዊ አውደ ጥናት በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይም የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ዋና ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ጤናው እንደገለጹት የከተሞችን የእርስ በርስ ትስስር በማጠናከር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ ነው።
በተለይም ከተሞች የውስጥ ገቢያቸውን በማሳደግ የህዘቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ሊመልሱ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የትብብር መድረኩ 108 አባል ከተሞችን በአባልነት መያዙን ጠቅሰው በመድረኩም ከተሞች ልምድ እየተለዋወጡ ለእድገታቸው የተሻለ ግብዓት እያገኙበት መሆኑን አስረድተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ የምስራች ገመዴ በበኩላቸው የትብብር መድረኩ እያደገ የመጣውን የነዋሪዎች የአገልግሎትና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተሻለ ልምድ የሚቀሰምበት መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ከተሞችን በማዘመን ለነዋሪዎች ምቹና ጽዱ ለማድረግ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻነታቸውን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ(ዶ/ር) በከተማው የኮሪደር ልማትና የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
በተጨማሪም የከተማዋን የገቢ አቅም ለማሳደግ የሚያግዙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችም እየተተገበሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ የ22 ከተማ ከንቲባዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026