
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 27/2017 (ኢዜአ)፡-ትውልዱ ከቀድሞ አባቶቹ ድል አድራጊነትን በመማር ድህነትን በመዋጋት የዘመኑ አርበኛነቱን ማረጋገጥ እንዳለበት አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአራተኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተሳታፊዎች ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አራተኛውን አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ በይፋ አስጀምረዋል።
በክህሎት ውድድሩ ስራቸውን ካቀረቡት መካከል ወርቅአፈራሁ ሻፊ እንዳለው፥ በውድድሩ በውጭ ምንዛሬ ወደ አገር ውስጥ ይገባ የነበረውን የሰብል መውቂያ ማሽን በፈጠራ በመስራት ማቅረባቸውን ተናግሯል።
ማሽኑ በሰዓት እስከ 15 ኩንታል እህል የሚወቃና ተረፈ ምርቱም ለከብቶች መኖ እንዲውል ማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ገልጿል።
በቆጮ አዘገጃጀት ላይ ፈጠራቸውን ይዘው የመጡ መምህር ተስፋዬ ታደሰ በበኩላቸው፥ከዚህ ቀደም እናቶች በባህላዊ መንገድ ቆጮን ሲያዘጋጁ ልፋትና እንግልት እንደሚገጥማቸው ያነሳሉ።
ይዘው የቀረቡት ቴክኖሎጂ የእናቶችን ችግር የሚያቃልል፣ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግና የቆጮ ጥራትን የሚያስጠብቅ መሆኑንም ተናግረዋል።
የፈጠራ ባለቤት ደምስ ኪዳኔ በበኩሉ፥ የሰሩት ማሽን የሽመናና የልብስ ምርትን ለማዘመን የሚያስችል ነው።
ማሽኑ በሞተሩ ውጭ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ግብዓት የተሰራ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ከሽመና በተጨማሪ የተለያዩ ልብሶችንና ጨርቆችን ማምረት የሚያስችል ነው።
የአርበኞች ቀን የቀድሞ አባቶቻችን ወራሪ ጠላትን ድል በመንሳት ነፃነትን የተቀዳጁበት መሆኑን አውስተው፤የአሁኑ ትውልድ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ ድህነትን መዋጋት አለበት ብለዋል።
የዘመኑ አርበኝነት ድህነት ላይ መዝመትን የሚጠይቅ በመሆኑ ትውልዱ የአገር ምርት በመጠቀም፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥና በምርምር የተደገፈ ስራ በመስራት ድህነትን መዋጋት እንደሚገባው ተናግረዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026