የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማዋን ውብ ገፅታ ያላበሱና የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የቀየሩ ናቸው

May 6, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ከተማዋን ውብ ገፅታ ያላበሱና የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የቀየሩ ናቸው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች አዲስ አበባን ዘላቂነት ባለው አግባብ ለዜጎች ምቹ እና ውብ እያደረጓት ይገኛል።


ልማቱ የከተማዋን ገፅታ ከመሰረቱ ከመቀየር ባሻገር ለነዋሪዎቿ ምቹና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን እያንደረደራትም ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን አስመልክቶ ከነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

አቶ ኤርሚያሰ ተገኔ በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ከተማዋን ውብ ገፅታ ያላበሱና የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የቀየሩ ናቸው ፣ ለሰው ልጆች ምቹ እና አስፈላጊ በሆነ መልኩ መገንባቱን ተናግረዋል።

የተገነቡት የመናፈሻ ቦታዎች፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች የራስን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳላቸው ነው የተናገሩት ።


የፈረንሳይ ለጋሲዮን ነዋሪ የሆነችው ሃይማኖት አብርሃም በበኩሏ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች ናቸው ብላለች።

በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች የተሰሩ የልማት ስራዎች እንዳይበላሹ ነዋሪዎች በሃላፊነት መጠቀም እና መንከባከብ እንዳለበት ተናግራለች።

አቶ ሀይለማርያም ኪዳኔ ለ40 አመታት በካዛንችስ አካባቢ መኖራቸውን ተናግረው ከዚህ ቀደም የነበረውን የአካባቢውን ገጽታ ሙሉ በሙሉ የቀየረና ውብ ገጽታ ያላበሰ ግንባታ መመልከታቸውን ተናግረዋል።


በካዛንቺስ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁና አስደናቂ ውበት የተላበሱ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።


እየተሰራ ያሉ ስራዎች ትውልድን ማዕከል ያደረጉ በመሆናቸው የሚበረታታ ነው ያሉት የመዲናዋ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዘላለም ጀምበሩ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026