
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 18/2017 (ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ ከተማ ነገ ለሚደረገው የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ለተሽከርካሪዎችና ለእግረኞች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የከተማዋ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡
የውድድሩ መነሻ ቦታ መስቀል አደባባይ ሲሆን ለገሃር መብራት፣ ቡናና ሻይ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አፍሪካ ህብረት ሳር ቤት (ፑሽኪን አደባባይ)፣ ቄራ አዲሱ መሿለኪያ ድልድይ፣ ጎተራ ማሳለጫ፣ አጎና ሲኒማ፣ ግሎባል ሆቴል፣ መስከረም ማዞሪያ፣ ጥላሁን አደባባይ፣ ሳንጆሴፍ መብራት አድርጎ መስቀል አደባባይ ያበቃል።
በዚህም መሠረት :-
* ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ )
* ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
* ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)
* ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
* ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሀር መብራት
* ከሠንጋ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
* ከአረቄ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
* ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
* ከልደታ ፀበል ወደ አፍሪካ ህብረት መብራት
* ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
* ከቫቲካን ወደ ሳርቤት አደባባይ
* ከቄራ አልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ መብራት
* ከጎፋ ገብርኤል አቅጣጫ ወደ ጎፋ መስቀለኛ በስር
* ከዮሴፍ ወደ ጎተራ ማሳለጫ
* ከመስቀል ፍላዎር ወደ አጎና መስቀለኛ
* ከጋዜቦ አደባባይ ወደ በቅሎ ቤት ድልድይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ይዘጋሉ።
በተጠቀሱት መስመሮችም ከዛሬ ምሽት 12 ሠዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026