
ባህርዳር፤ ሚያዚያ9/2017(ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከአልማ እስከ ዋተር ፍሮንት ሆቴል የሚካሄድ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ዛሬ ተጀምሯል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት የተጀመረው የፕሮጀክቱ ግንባታ 800 ሜትር ርዝመትና 40 ሜትር ስፋት ያለው አስፋልት መንገድ እንደሆነ ተመልክቷል።

መንገዱ ጣና ሀይቅን በቀጥታ ከከተማው የሚያገናኙ ከመሆኑም በላይ የከተማዋን ውበት፣ የቱሪስትና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት ይበልጥ የሚያሳድግ እንደሆነ በሥነ-ሥርዓቱ ለይ ተነግሯል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የ3 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እየተፋጠነ ሲሆን በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።
የኮሪደር ልማቱ የአረንጓዴ ልማት፣ የእግረኛ መንገድ፣ የብስክሌት መንገድና ሌሎች ልማቶችን አካቶ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
በማስጀመሪያው ሥነ-ሥርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች አመራር አባላትና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026