
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 2/2017(ኢዜአ)፡- አዲስ አበባን ውብ እና ጽዱ በማድረግ ሂደት ላይ አሻራችንን በማኖራችን ኩራት ይሰማናል ሲሉ የኮሪደር ልማት ሰራተኞች ገለጹ።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የመንገድ፣ የመብራት፣ የቤት ግንባታ እና እድሳት እንዲሁም ሌሎች የልማት ተግባራትን በማከናወን መዲናዋን ትርጉም ባለው መልኩ ማስዋብ እና ማሳመር ተችሏል፡፡
የሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የወንዝ ዳር ልማቶችን ጨምሮ በስምንት የተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመከናወን ላይ የሚገኘውን የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴ ትናንት ምሽት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ከንቲባዋ በኮሪደር ልማቱ እየተሳተፉ የሚገኙ ሰራተኞችን በማበረታታት የእራት ግብዣ አድርገዋል።
የልማት ስራዎቹን በተቀመጠላቸው ጊዜ እና ጥራት ለማጠናቀቅ ሳምንቱን ሙሉ ቀን ከሌት ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በምሽት የኮሪደር ልማት እየተሳተፉ ከሚገኙ ሰራተኞች መካከል ሳሙዔል አዲሱ ለኢዜአ በሰጠው አስተያየት፤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስራ ቦታችን ተገኝተው ስላበረታቱን ከፍተኛ ደስታ ተስምቶናል ብሏል።
ጉብኝቱ ይበልጥ ለስራ እንዲበረቱና ልማቱን በተያዘለት እቅድ ለማጠናቀቅ እንዲተጉ የሞራል ስንቅ እንደሆናቸውም ገልጿል።
እኛም አዲስ አበባ ከተማን ውብ እና ጽዱ በማድረግ ሂደት ላይ አሻራችንን በማኖራችን ኩራት ይሰማናል ነው ያለው።
ሌላኛዋ የኮሪደር ልማት ሰራተኛ መዲካ ከበደ በበኩሏ፤ የኮሪደር ልማቱ ለእናቶች፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግራለች፡፡
ከንቲባዋም በየጊዜው እየመጡ ሰራተኞችን እንደሚያበረታቱ እና ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው አንስታለች።
አዲስ አበባ ከተማን ለማስዋብ በሚደረግ ጥረት የበኩሌን አስተዋጽኦ እየተወጣሁ በመሆኑ ክብርና ደስታ ይሰማኛል ያለችው ደግሞ ሌላዋ በኮሪደር ልማቱ ስራ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ሜላት አበበ ናት፡፡
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026