የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ በዲጂታል ማንነት ዓለም አቀፍ የአመራርነት እውቅና አገኙ

Apr 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2017(ኢዜአ)፡- የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ በዲጂታል ማንነት ባሳዩት የአመራርነት ሚና ኦክታ ከተሰኘ የአሜሪካ ኩባንያ ዓለም አቀፍ እውቅና አግኝተዋል።

ዋና መቀመጫውን በአሜሪካ ሳን ፍራንሲስኮ ያደረገው ኩባንያ አቶ ዮዳሔን በዓለም ደረጃ በዲጂታል ማንነት የአመራርነት ሚና ካላቸው 25 ሰዎች አንዱ በሚል እውቅና ሰጥቷቸዋል።

በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም መርሃ ግብር 12 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መመዝገባቸውንና ይህን ቁጥር እ.አ.አ በ2025 ላይ 45 ሚሊዮን ለማድረስ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ኩባንያው ገልጿል።

አጠቃላይ 90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በፋይዳ መታወቂያ ተደራሽ የማድረግ እቅድም ተይዟል።


የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ የዲጂታል ማንነት ሁሉም ቦታ ተደራሽ የመሆን፣ የዜጎችን ኑሮ የመቀየር እና አካታችነትን የማረጋገጥ ሰፊ አቅም እንዳለውም አመልክተዋል።

የፕሮግራሙ ግብ ዜጎችን መመዝገብ ብቻ አይደለም የሚሉት አቶ ዮዳሔ በመታወቂያው ዜጎች እያገኙ ያለው አገልግሎት ስራችን ከሌላው የተለየ ያደርገዋል ሲሉም ተናግረዋል።

ለማህበረሰቡ እና ተቋማት ግንዛቤ መፍጠርን ጨምሮ ሌሎች የነበሩ ፈተናዎችን በማለፍ በፕሮግራሙ አስገራሚ ለውጦች መገኘታቸውን አመልክተዋል።

የፋይዳ የቴክኖሎጂ እና ህጋዊ ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር የተከናወነው ስራ ትልቅ ውጤት የተገኘበት ነው ብለዋል።

ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥን እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል።

ኦክታ እ.አአ በ2009 የተቋቋመ በዲጂታል ማንነት እና መረጃ አስተዳደር ላይ የሚሰራ የአሜሪካ ኩባንያ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026