
ሚዛን አማን፣መጋቢት 7/2017 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሠላምን በማፅናት ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።
በሠላምና ልማት ዙሪያ የሚያተኩር የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።
ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳደሩ እንዳመለከቱት፥ ባለፉት ሦስት ዓመታት ተኩል በክልሉ የሠላም ግንባታ፣የልማትና፣የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ሲከናወኑ ቆየተዋል።
በዚህም ውጤት መገኘቱን ገልጸው፥በተለይ በምዕራብ ኦሞ ዞን ከፀጥታ ጋር ተያይዞ የነበረው ችግር እየተፈታ ለልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።
ይህን አጠናክሮ በማስቀጠልና ሠላምን በማፅናት ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልል በተለይ የዞኑን ሠላም በማስጠበቅ ልማትን ለማጠናከር በሚቻልበት ላይ ዛሬ እየመከረ ያለው መድረክ በተመሳሳይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
በአማን ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ የክልሉና የምዕራብ ኦሞ ዞን አመራር አባላት እንዲሁም ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026