
መቱ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- በኢሉአባቦር ዞን ቡና ከማሳ እስከ ገበያ ጥራቱን ጠብቆ እንዲቀርብ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት እንዳለባቸው የዞኑ አስተዳደር አስገነዘበ።
ባለሀብቶች እና ነጋዴዎች የተሳተፉበትና በቡና ጥራትና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በመቱ ከተማ ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንደገለጹት የቡና ጥራትን ለማረጋገጥ ከማሳ እስከ ገበያ ድረስ እየተሰሩ በሚገኙ ሥራዎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ነው።
ይሁን እንጂ አሁንም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁመው፣ በየዓመቱ ከዞኑ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበው ቡና ከአጠቃላይ ዓመታዊ ምርት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
በመሆኑም ቡና አምራቾች፣ ነጋዴዎችና አቅራቢዎች ለቡና ጥራቱ የበኩላቸውን ድርሻ ከመወጣት ባሻገር ሕገ-ወጥ የቡና ንግድን ጨምሮ በጥራት ላይ ችግር የሚያስከትሉ ነገሮችን በጋራ መከላከል ይገባል ብለዋል።

የቡና ገበያ ከዓለም አቀፍ ነባራዊና ተለዋዋጭ ሁኔታ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነጋዴዎችም ቡናን በተገቢው ጊዜ ለገበያ ማቅረባቸው ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግና እንደሀገር የሚጠበቀውን ጥቅም ማግኘት የሚያስችል መሆኑም ከግንዛቤ ማስገባት አለባቸው ነው ያሉት።
በቡና ልማት ዘርፍ ያለው የኢንቨስትመንት ሁኔታም ትኩረት የሚሻ በመሆኑ ባለሀብቶች ከመንግስት ጋር በቅርበት እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ጥራቱ የተረጋገጠ ቡና ለገበያ ለማቅረብ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ብዙ እንደሚጠበቅና የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ከተሳታፊዎቹ መካከል አቶ ዴሬሳ ተሰማ፣ ሕገ-ወጥ የቡና ንግድን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ደካማ መሆን ለቡና ጥራት ችግር መንስኤ እንደሆነ አንስተዋል።
በመስኩ ለሚሰማሩ አካላት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚደርገው ጥረት መጠናከር እንዳለበትም አመልክተዋል።
የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰጠው ትኩረት ለጥራቱም መሰጠት እንዳለበት ያነሱት ሌላው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ ፈቀደ ማሞ ናቸው።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026