
መቀሌ፤መጋቢት 5/ 2017 ( ኢዜአ)፡-በትግራይ ክልል ለ300 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችሉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ዝግጁ መሆናቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ።
በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ስልጠና ካቢኔ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አልጋነሽ ተሰማ (ዶ/ር)፤ለ300 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችሉ በግብርና፣ማኑፋክቸሪንግ፣ አነስተኛ ኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ለስራ እድሉ ከተመቻቹ ፕሮጀክቶች መካከል መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
በክልሉ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና በግል ከሚሰሩ ምሁራን ጋር በመተባበር የኢንተርፕራይዞች ፕሮጀክቶች ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑንም ተናግረዋል።
በፕሮጀክቶቹ ከ420 የሚልቁ የልማት ዘርፎችን ያቀፉ ኢንተርፕራይዞች እንደተካተቱም ኃላፊዋ ገልጸዋል።
በቀጣዮቹ ወራትም 100 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ104 ቢዝነስ ኢንተርፕራይዞች ዝርዝር የትግበራ እቅድ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል።
በፕሮጀክቱ ከተካተቱ የቢዝነስ ዓይነቶች ውስጥ የወተት እና ወተት ተዋፅኦ፣የንብ ማነብና የማር ምርት፣ የበለስና የእንጉዳይ ምርቶችን ጨምሮ ሌሎችም መኖራቸውን ዘርዝረዋል።
በእውቀት ላይ የተመሰረቱ የልማት ኢንተርፕራይዞችን ማደራጀትና ተግባራዊ ማድረግ ከድህነት ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር ወሳኝ በመሆኑ በሚቀጥሉት ወራት ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026