
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት በትብብር መስራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርዓያሥላሴ ናቸው።

ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) የመግባቢያ ስምምነቱ የብሔራዊ መታወቂያ(ፋይዳ) አጠቃቀምን ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስራዎች ጋር የሚያስተሳስር መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ይህም ተቋማቱ አገልግሎትን ቀልጣፋ ግልጽና ፍትሃዊ ለማድረግ፣ የትራንስፖርት ደህንነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሌብነትና ማጭበርበርን መከላከል የሚያስችል ስራ በተቀናጀ አግባብ ለመስራት እንደሚያስችላቸው አመልክተዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026