
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ500 ሚሊዮን ብር ካፒታል ከበቆሎ ምርት ስታርች ለማምረት ስራ የጀመረው ሀገር በቀል ኩባንያ የማሽን ተከላ ስራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራ ምርት ማምረት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
የባህር ዳር ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ጥሩየ ቁሜ እንደገለጹት ኩባንያው 2 ሄክታር መሬት ተረክቦ የግንባታ እና የማሽን ተከላ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

ኩባንያው ከ4000 በላይ ከሚሆኑ አርሶ አደሮች ጋር ዘላቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖረው የሚያስችል የገበያ ትስስር ፈጥሯልም ነው ያሉት፡፡
ኩባንያው ምርቱን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ለኮርፖሬሽኑ መግለጹንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ፓሮን ትሬዲንግ 592,000 ኩንታል በቆሎን በግብዓትነት የሚጠቀም መሆኑን ገልጸው ይህም ለአካባቢው በቆሎ አምራች አርሶ አደሮች ቀጣይነት ያለው ገበያ ትስስር ከመፍጠሩ በተጨማሪ በስራ እድል ፈጠራ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት፡፡
ኩባንያው አሁን ላይ ለ300 የአካባቢው ወጣቶች ዘላቂ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ማለታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ይጠቁማል፡፡
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026