
አዲስ አበባ፤መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፦የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን በማላመድ አረንጓዴ ልማትን ለመገንባት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለፁ።
በኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች ማስፈፀሚያ ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ስትራቴጂውን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በጋራ እንዳዘጋጁት በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዚሁ ወቅት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።
የትራንስፖርት ዘርፉ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ለስኬታማነቱ ዘርፉን የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ታዳሽ ሃይል የአየር ብክለትን ከመቀነስ ባለፈ ለነዳጅ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታ ለማዋል ያስችላል ነው ያሉት።
ከተሞችን ፅዱና ስማርት ለማድረግ የጎላ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፥ ለዚህ ደግሞ የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን ማስፋፋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ይህን ለማሳካት የሁሉንም ቅንጅት የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
መድረኩ የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች ማስፈፀሚያ ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ ከመወያየት ባለፈ ወደ ተጨባጭ ስራ ለመግባት የሚያስችል መሆኑንም አስታውቀዋል።
በዚህም ታዳሽ ኃይል የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ስራ ላይ ለማዋል የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026