
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት የወተት ምርታማነትን ለመጨመር ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በወተት ልማት የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በልማቱ የተሰማሩ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት በዓለም አቀፍ እንስሳት ጥናት ኢንስቲትዩት(ILRI) ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ(ዶ/ር) መንግስት የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ብሔራዊ ፕሮግራም ተቀርፆ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የወተት ምርትን የሚመራ፣ በምርምር የሚደግፍ፣ የተበጣጠሱ ስራዎችን በጋራ መስራት የሚያስችል፣ ከሌሎች ሀገሮች ተሞክሮዎችን በመቅሰም በሀገር ውስጥ ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያግዝ ቦርድ በመድረኩ እንደሚቋቋምም ጠቁመዋል።
መንግስት የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዝርያ ማዳቀል፣ መኖ ማልማት፣ ወተት ማቀነባበር እና ገበያ ማስተሳሰር ላይ ያሉ ስራዎችን መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል፡፡
የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ከመቀረፁ በፊት 5 ነጥብ 8 ቢሊየን ሊትር ወተት በዓመት ይመረት እንደነበር አስታውሰው በዘንድሮ የምርት ዘመን ከ12 ቢሊዮን ሊትር በላይ ወተት ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስራት ጤራ(ዶ/ር) በበኩላቸው በሌማት ትሩፋት ፕሮግራም የተገኙ ስኬቶችን የተመለከተ ሰነድ አቅርበው በፕሮግራሙ የተመዘገቡ ለውጦችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአለም አቀፍ እንስሳት ጥናት ኢንስቲትዩት(ILRI) ዋና ዳይሬክተር ናሙኮሎ ኮቪክ በወተት ልማት ላይ ለተሰማሩ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ መዘጋጀቱ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
ውይይቱ እስከ ነገ እንደሚቆይ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026