የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በክልሉ የክላስተር ማዕከላት አገልግሎት መስጫ ህንጻዎች ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃግብር እየተካሄደ ነው

Mar 10, 2025

IDOPRESS

ሆሳዕና ፤የካቲት 30/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰባቱም የክላስተር ማዕከላት አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በከተሞቹ እየተካሄደ ነው፡፡

በክልሉ የክላስተር ማዕከላት በሆኑ በሆሳዕና፣ ቡታጅራ፣ ወራቤ፣ ወልቂጤ፣ ቁሊቶ፣ ዱራሜና ሳጃ ከተሞች የአገልግሎት መስጫ ህንፃዎቹ ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በሆሳዕና ተገኝተው የአገልግሎት መስጫ ማዕከሉን ግንባታ በማስጀመር ላይ ይገኛሉ።

ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነቡት የሰባቱም የክላስተር ማዕከላት ህንፃዎች ግንባታ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉም ተጠቁሟል፡፡


የቢሮዎቹ ግንባታ ለቢሮ ኪራይ የሚወጣን ወጪ በማስቀረትና ለሌላ ልማት በማዋል የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም እንዲሁ፡፡

የግንባታ ስራው በሚፈለገው ጥራትና በታቀደለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ተገቢ የሆነ ክትትል እንደሚደረግም በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ሂደትና አፈጻጸም ክትትል በተመለከተ ሰነድ እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ርዕሰ መስተዳድሩና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ግንባታውን በይፋ ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ እና የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የሀድያ ዞንና የሆሳዕና ከተማ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026