
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- በከተማ ግብርና ከራሳቸው ባለፈ ለበርካቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻላቸውን በመዲናዋ በከተማ ግብርና ስራ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከመደበኛው ግብርና በተጨማሪ በከተማ ግብርና ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በዚህም በመዲናዋ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በእንስሳትና ዶሮ እርባታ እንዲሁም በንብ ማነብ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም ይታወቃል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማ ግብርና ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ምርቶቻቸውን ለህብረተሰቡ እያቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።
ከሸማችነት ወደ አምራችነት በመሸጋገር የኑሮ ውድነት ጫናን ማቃለል እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጠው የከተማ ግብርና ተጠቃሚው አቶ መኮንን አለሙ አንዱ ማሳያ ናቸው።
በዘርፉ የሚያገኙት ምርት ከፍጆታቸው ባለፈ ለገበያ በማቅረብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም 15 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር መቻላቸውን ተናግረዋል።

ሌላው በከተማ ግብርና ተጠቃሚ የሆነው ሲሳይ አለሙ በበኩሉ በከተማ ግብርና ከተሰማራ ወዲህ ከሸማችነት መውጣቱን ገልጿል።
በዚህም ከራሱ ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብም የአትክልት እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን እያቀረበ እንደሚገኝ ተናግሯል።
የስራ እድል የተፈጠረላቸው ግለሰቦችም በሚያገኙት ገቢ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን እየደገፉ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ የከተማ ግብርና ከዕለት ፍጆታ እስከ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።
በመዲናዋ እስካሁን በተሰራው ስራ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በአነስተኛ ቦታ ላይ አትክልት በማልማት የምግብ ፍጆታቸውን በራሳቸው እንዲሸፍኑ እንዲሁም ለገበያ በማቅረብ ገቢያቸው እንዲያድግ መደረጉን ጠቅሰዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026