የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

<p>ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለአፍሪካ ንግድና ቱሪዝም ትልልቅ ዕድሎችን የሚከፍት ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ</p>

Mar 3, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤የካቲት 23/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል ከኢትዮጵያ ባለፈ ለአፍሪካ ንግድና ቱሪዝም ትልልቅ ዕድሎችን የሚከፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።


አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ስነስርዓቱ ወቅት እንዳሉት፤አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን የሚያጎሉ ፕሮጀክቶችን ቀርጻ እውን እያደረገች ነው።


የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የነገዋ ሴቶች ተሃድሶና የልህቀት ማዕከል እንዲሁም ብርሃን ማየት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ባለፈው አንድ ዓመት እውን የሆኑ ስኬታማ ፕሮጀክቶች ናቸው ብለዋል።


የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልም የአዲስ አበባን ብሎም የአፍሪካን ተወዳዳሪነት ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑንም አብራርተዋል።


ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለአፍሪካ ትልልቅ እድሎችን የሚከፍት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፥ ለቀጣናዊ ንግድ ትስስር መጠናከር፣ ጎብኝዎችን ለመሳብ እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ አወንታዊ ሚና አለው ብለዋል።


ማዕከሉ የቢዝነስ ውይይቶችና የስምምነት መርሃ ግብሮችን ለማካሄድ፣ ልዩ ልዩ ኤግዚቢሽኖችና ባህላዊ መድረኮችን በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም ያለው መሆኑንም አስረድተዋል።


ሀገራዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ለተጀመረው ጉዞ የማዕከሉ እውን መሆን ዓይነተኛ ሚና እንደሚያበረክትም ነው ከንቲባ አዳነች የገለጹት።


በመሆኑም የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ የልማት ድርጅቶች በማዕከሉ ያላቸውን ድርሻ በማሳደግና የተፈጠረውን ዕድል በመጠቀም ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር አለባቸው ብለዋል።


ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማሳለጥ ሰፋፊ የልማት ሥራዎች በማከናወን እና የፕሮክጀክቶችን አፈጻጸም በማሻሻል ላይ ትኩረት መደረጉንም አንስተዋል።


የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በድል በመሻገር በትጋትና በታማኝነት ሥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል።


አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል 40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በድምሩ እስከ 10 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሁለት ትላልቅ እና 8 መካከለኛ አዳራሾችን ያካተተ ነው።


ባለ 5 ኮከብ ሆቴል፣ሬስቶራንቶች፣መዝናኛና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ በአንድ ጊዜ 2 ሺህ ተሽከርካሪ ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026