
ሮቤ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- በባሌ ዞን የቡና ልማትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዘንድሮ የሚተከል ምርጥ የቡና ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የቡና ችግኞቹ ከግብርና ምርምር ማዕከላት የተለቀቁና በሽታን በመቋቋም የተሻለ ምርት የሚሰጡ መሆኑም ተመልክቷል።

በጽህፈት ቤቱ የቡና ጥራት ባለሙያ አቶ ሰለሞን ጋረደው ለኢዜአ እንዳሉት፣ በዞኑ እስካሁን የቡና ልማትና ምርታማነትን ለማሳደግ 36 ነጥብ 2 ሚሊዮን ምርጥ የቡና ችግኝ ለተከላ ተዘጋጅቷል።
የቡና ችግኞቹ የሚተከሉት በዞኑ የቡና አብቃይ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ነባር የቡና ማሳና ከ14 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ አዲስ መሬት ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
ምርጥ የቡና ችግኞች ከጅማ፣ መቻራና ሲናና ግብርና ምርምር ማዕከላት የተገኙትን ጨምሮ 15 የተሻሻሉ የአካባቢ ዝርያዎች ያካተቱና በሽታን ተቋቁመው የተሻለ ምርት የሚሰጡ ናቸው።
በአካባቢው ከሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚገባውን የበልግ ዝናብ በመጠቀም የሚተከሉት እነዚህ የቡና ችግኞች በመንግስትና የግለሰብ የችግኝ ጣቢያዎች ላይ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ነው የተናገሩት።
የቡና ዝርያዎቹ ከነባሩ የአካባቢ ዝርያ በሄክታር በአማካይ የሚገኘውን ሰባት ኩንታል ምርት ወደ 10 ኩንታል የማሳደግ አቅም አላቸው ብለዋል።
በዞኑ አዲዲስ የቡና ችግኞችን ለማስፋፋት እየተደረገ ከሚገኘው ጥረት በተጓዳኝ ያረጁና ከምርት ውጭ የሆኑ የቡና ተክሎችን የማደሱ ሥራ ጎን ለጎን እየተሰራ መሆኑንም አስታውሰዋል።
በዚህም በዞኑ ከ1 ሺህ 450 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ያረጃ ቡና የማደስ ሥራ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።
በባሌ ዞን በአሁኑ ወቅት ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በቡና ተክል የተሸፈነ መሆኑን ከዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026