
አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ በ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት በሰው ተኮርና በጎ ፈቃድ አገልግሎት 1 ሚሊዮን 197 ሺህ 413 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች በመዲናዋ ባለፉት ስድስት ወራት በየዘርፉ የተያዙ እቅዶችን አፈጻጸም ለምክር ቤቱ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በዚህም የበጎ ፍቃድና ሰው ተኮር አገልግሎት ለዘላቂ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
በመዲናዋ የተለያዩ ቦታዎች በተቋቋሙ 24 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በየቀኑ 36 ሺህ ለሚደርሱ ወገኖች የምገባ መርሃ ግብር እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።
እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች፣ አረጋዊያን፣አቅመ ደካሞች፣ የአገር ባለውለታዎችን ጨምሮ 3 ሺህ 737 ቤቶችን በመገንባት 20 ሺህ 484 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አመልክተዋል።
ከቤት ልማት አኳያም በመንግሥት አስተባባሪነት፣ በግል አልሚዎችና በሪል ስቴት አማራጮች 27 ሺህ 304 ቤቶች መገንባታቸውንም ጠቅሰዋል።
በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ሁለተኛው የኮሪደር ልማት ሥራ ስኬታማ በሆነ መልኩ መከናወኑን ያነሱ ሲሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት ለሚነሱ ዜጎችና የንግድ ተቋማት ምትክ ቦታ መሰጠቱን ተናግረዋል።
ለልማት ተነሺዎች የመኖሪያ ቤቶች እንዲሁም መሥሪያ ሼዶች ተደራሽ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
አረንጓዴ ቦታዎች፣ የጤናና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ተግባራት መከናወናቸውን ነው ከንቲባ አዳነች የገለጹት።
እንደ ከንቲባ አዳነች ገለጻ በብዙሃን ትራንስፖርት አቅርቦት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የትራንስፖርት አቅርቦትን የማሳደግ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
ለአብነትም ባለፉት ስድስት ወራት 100 አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው በቀን 1 ሺህ 408 አውቶብሶችን በማሰማራት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም አብራርተዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026