
ጊምቢ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፡- ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዝርያቸው የተሻሻለ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው የተቀናጀ ግብርና ምርምር ማዕክል ዳይሬክተር ሶሬሳ ሹማ፤ ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከጅማና ሌሎች ግብርና ምርምር ማዕከላት በምርምር የተገኙ 12 አይነት የቡና ዝርያዎችን በማላመድና በማባዛት በመጪው ግንቦት ወር ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት ተዘጋጅቷል።
ለስርጭትየተዘጋጁት የቡና ችግኝ ዝርያዎች በሽታን ተቋቁመው በሄክታር ከ14 ኩንታል በላይ ምርት የሚሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቡና ዝርያዎቹ ከ2 እስከ 3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ምርት የሚሰጡ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
የቡና ችግኞቹ በቄለምና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች እንደሚሰራጩ አስታውቀዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026