
ታርጫ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከአዝርትና ሆርቲካልቸር ሰብሎች ከ40 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ባለው የምክር ቤት ጉባኤ የአስፈፃሚ ተቋማት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን ሲያቀርቡ እንደገለጹት፣ ምርቱ የተሰበሰበው በመኸር እርሻ ከለማው ነው።
በእርሻና በእንስሳት ዘርፍ የሚፈለገውን ውጤት ለማግኘት በቅንጅት በተሰራ ሥራም አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በመኸር አዝመራ ከለማው 384 ሺህ 786 ሄክታር መሬት ከ17 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል።
ከዚህ ውስጥ 90 ሺህ 297 ሄክታሩ በክላስተር የለማ መሆኑን አስታውሰው፣ ይህም አምራቾች ከክላስተር ልማት የተሻለ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ልምድ ያገኙበት መሆኑን ተናግረዋል።
ከ159 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ሆርቲካልቸር፣ አትክልትና ሥራሥር እንዲሁም እንሰት በማልማት 23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ነው ያስረዱት።
የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ በግማሽ በጀት ዓመቱ 146 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ የአፈር ማዳበሪያ ተሰራጭቷል ብለዋል።
ከ31 ሺህ በላይ እንስሳትን በማዳቀል አርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀው፤ ከ12 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ ማሳ ላይ የመኖ ልማት ሥራ ተከናውኗል ብለዋል።
ባለፈ የተሻለ ምርት የሚሰጥ የቡና ዝርያ ችግኝ ዝግጅት ሥራ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ በ13 ሺህ 535 ሄክታር ማሳ ላይ አዳዲስ የቅመማ ቅመም ልማት ችግኝ ተከላ ሥራ መከናወኑን አስታውቀዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት የማር ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት ከ57 ሺህ በላይ ዘመናዊ፣ የሽግግርና ጨፈቃ ቀፎች መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026