የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

<p>ዩኒየኑ አርሶ አደሮችንና ሸማቹን ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመራቸውን ሥራዎች እንደሚያጠናክር አስታወቀ</p>

Feb 10, 2025

IDOPRESS

መተማ፤ የካቲት 1/2017 (ኢዜአ)፡-መተማ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን አርሶ አደሮችንና ሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

ዩኒየኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በገንዳውሃ ከተማ አካሄዷል።


የዩኒዬኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብቴ ዘውዱ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ዩኒየኑ በዞኑ ሦስት ወረዳዎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች 47 ማህበራትንና 29 ሺህ የሚጠጉ አርሶ አደሮችን አቅፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በዚህም ለአርሶ አደሮች ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ ፀረ አረም፣ የእንስሳት መድኃኒት እና መሰረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች የኑሮ ጫና ለማቃለል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያውን እያረጋጋ መሆኑንም ተናግረዋል።

የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ዩኒየኑ ትኩረት ስጥቶ ሲሰራ መቆየቱንም አስታውሰዋል።

ለእዚህም በዓመት ከ40 ሺህ ኩንታል በላይ ሰሊጥ ማበጠር የሚችል የሰሊጥ ማበጠሪያ ማሽን ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በቀጣይም የጥጥ መዳመጫና የዘይት ፋብሪካ ለማቋቋም ዕቅድ መያዙን ጠቅሰው፣ አርሶ አደሮችንና ሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሕብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በልጣ ጌትነት በበኩላቸው እንዳሉት፣ ዩኒየኑ ካለው የሰው ሀይልና ሀብት የተነሳ አገልግሎቱን ይበልጥ ማጠናከር ይኖርበታል።

ዩኒየኑ ባለው የሰሊጥ ማበጠሪያ ማሽን ሰሊጥን እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት እየደገፈ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዩኒየኑ ካፒታል በማሳደግ የአባላቱንና የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እየሰጣቸው ያሉ አገልግሎቶችን ማሳደግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

አርሶ አደር አምባው ገብረእግዚአብሔር በመተማ ወረዳ የኮኪት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ዩኒየኑ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ግብአትን ከማቅረብ ጀምሮ ለእንስሶቻቸው የጤና አገልግሎት እየሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እየሆነ መጥቷል ያሉት አርሶ አደሩ፣ የግብርና ግብአቶችን ተጠቅመው ማልማት ከጀመሩ ወዲህ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መሆኑንን ገልጸዋል።

የገንዳውኃ ከተማ ሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበር አመራር አቶ ሙሉዓለም ጌታሁን በበኩላቸው፣ ዩኒየኑ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ከሌላ አካባቢ በማምጣት ለሸማቹ በማድረስ ገበያ የማረጋጋት ሥራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መተማ የገበሬዎች ሁለገብ የሕብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን በ1992 ዓ.ም በ52 ሺህ ብር ካፒታል የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ሀብቱ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025