አዲስ አበባ፤ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ወራት ህገ-ወጥ እና አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከል በተሰሩ ሥራዎች ከጨረታና ከቅጣት ከ 135 ሚሊዮን ብር መገኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ባለሥልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በየደረጃው ካሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
በመድረኩ ከመዲናዋ 11 ዱ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፥ባለስልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ የደንብ ጥሰቶችን ጨምሮ አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተው የተወረሱ ንብረቶችን በጨረታ በመሸጥ 12 ሚሊየን ብር እንዲሁም ህግ በተላለፉ አካላት ላይ ከተጣለ ቅጣት 123 ሚሊየን ብር በአጠቃላይ 135 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡
በተለይም ህገ-ወጥ ግንባታዎችና የጐዳና ላይ ንግድ እንዲሁም አዋኪ ድርጊቶችና ሌሎች ደንብ መተላለፎችን በመከላከል በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል።
በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎች የደንብ መተላለፍን ለመቀነስና ለመከላከል ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበራቸው ተናግረዋል፡፡
ባለሥልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት የተቋም ግንባታ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራቱን ጠቅሰዋል፡፡
በመዲናዋ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ስራዎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እና ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምባቸው ሰፊ የጥበቃ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ በመዲናዋ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ ለመጠበቅና ህግ የሚተላለፉ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ከባለስልጣኑ ጎን በመቆም እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
በዚህም የደንብ መተላለፎችን በመከላከል የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጡ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025