
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፡- ህገ-ወጥ ሞተር ሳይክሎችን ወደ ህጋዊ መስመር ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የሲዳማና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ገለፁ።
በህገወጥ ሞተር አሽከርካሪዎች የተነሳ የሚደርሰው አደጋ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱ ይገለጻል፡፡
አደጋዎቹ በዋናነት መንጃ ፍቃድ በሌላቸውና በህገወጥ ሞተር ተጠቃሚዎች የሚደርስ መሆኑ ደግሞ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከፍ ያደርገዋል፡፡
ሰሌዳ አልባ ሞተር ሳይክልና መንጃ ፍቃድ የሌላቸው አሽከርካሪዎችን ወደ ህጋዊነት ለማስገባት በሲዳማና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የተጠናከረ ስራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
ኢዜአ የሲዳማና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊዎችን ህገ-ወጥ የሞተር ሳይክል ተሽከርካሪዎችን ወደ ህጋዊነት ለመመለስ እየሰሩ ባሉት ስራዎች ዙሪያ አነጋግሯል።
የሲዳማ ክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ታምሩ ታፌ እንዳሉት ሞተር ሳይክሎች በክልሉ በገጠር አካባቢዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ለወጣቶች የስራ እድል እየፈጠሩ ነው።
ሞተር ሳይክሎቹን እድሜያቸው ያልደረሰ ለጋ ታዳጊዎች እንደሚያሽከረክሯቸው ገልጸው ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ ያደረገው ትርፍ በመጫን ከፍጥነት በላይ መጓዛቸው ነው ብለዋል።
በዚህም በክልሉ አብዛኛው የትራፊክ አደጋ በሞተር ሳይክል እንደሚደርስ በመጠቆም ችግሩን ለመፍታት ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ጋር መፍትሄ ለማበጀት እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በክልሉ ከ40ሺህ በላይ ህገ-ወጥ ሞተር ሳይክሎች መኖራቸውን ገልፀው ለአስተዳደርና በቀላሉ ለመድረስ እንዲመች በማህበር መደራጀታቸውን ተናግረዋል።
የተደራጁት የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ይህም ባለፉት ስድስት ወራት በሞተር ሳይክል የሚደርስ አደጋ በ49 ነጥብ 5 በመቶ እንዲቀንስ ማስቻሉን ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የትራንስፖርት ዘርፍ ሃላፊ ብርሃኑ ጌቦ(ዶ/ር) በክልሉ ካሉ ሞተሮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ህገ-ወጥ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ህገ-ወጥ የሞተር ሳይክሎች ህጋዊ ሂደት እንዲከተሉ ለማድረግ በክልሉ ያሉ ሞተሮችን የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ህገ-ወጥ ሞተር ሳይክሎችን ከመመዝገብ ባለፈ ወደ ህጋዊ አሰራር ለማምጣት እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025