የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

<p>ለወጣቶችና ሕጻናት ምቹ የዲጂታላይዜሽን ምህዳር እየተፈጠረ ነው - ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) </p>

Jan 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ)፡- መንግሥት ወጣቶችና ሕጻናት በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ቁልፍ ተዋናይ የሚሆኑበት ምቹ ምህዳር እየፈጠረ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ የትምህርትና ውድድር ማዕከል ጋር በመተባበር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ሲያሰለጥናቸው ለነበሩ ተማሪዎች የዕውቅና ሰጥቷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) መንግስት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች በማሰልጠን ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ጉዞ ዋና ተዋናይ እንዲሆኑ ምቹ ምህዳር እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በርካታ ወጣቶች በተለያዩ ዓለማት በቴክኖሎጂና በፈጠራ ተወዳዳሪ ሆነው ሀገራቸውን ማስጠራት ጀምረዋል ነው ያሉት።

መንግስት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ የግሉ ዘርፍም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የኢትዮ ሮቦ ሮበቲክስ መስራችና ዋና ስራ አስከያጅ ሰናክሪም መኮንን ስልጠናው ወጣቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ አተገባበርን በመማር ሮቦትን እንዲቀርጹ የሚያደርግና በሮቦት ኮዲንግና እና ፕሮግራሚንግ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገልጸዋል።


ዕውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በሮቦቲከስ ፕሮግራሚንግና ኢንጅነሪንግ ሰልጥነው በቻይና ሀገር በተካሄደ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውድድር ላይ በመሳተፍ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ የነበሩ እንደሆኑ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025